ክረምት ገባ… ፍርድቤት ተዘጋ … ምን ያህል ያስኬዳል?

የፌደራል ፍ/ቤቶች የ2015ዓ.ም የመጨረሻ ቀጠሮዎቻቸውን ባሳለፍነው አርብ ሐምሌ 29 ቀን አስተናግደው ለክረምቱ ክፍለጊዜ ተዘግተዋል፡፡ እስከ ቀጣዩ አመት የመስከረም ወር መጨረሻ ድረስም ከተወሰኑ ተረኛ ችሎቶች በስተቀር መደበኛ ችሎቶች ዝግ ሆነው ይቆያሉ፡፡ በቀጣይ ሁለት ወራት እንደ ቀለብ ጥያቄ፣ የእግድ ይሰጥልኝ እና ሌሎች አስቸኳይ አቤቱታዎችን እና የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ተረኛ ችሎቶች በስተቀር ብዙሃኑ ችሎቶች ዝግ ሆነው ይቆያሉ፡፡ በክረምቱ ክፍለጊዜ አዲስ የክስ መዝገቦች በየችሎቱ መከፈታቸው የሚቀጥል ቢሆንም ቀጠሮ የሚያዝላቸው በቀጠዩ የ2016 ጥቅምት እና ሕዳር ወራት እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፍርድቤቶች ዘወትር በክረምት ወቅት በነሀሴ እና መስከረም ወር ዝግ የሚሆኑበት ምክንያት ቀደም ብሎ ግብርና በኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ ካለው ቦታ አንፃር አርሶአደሩ ዘወትር ዘሩን በሚዘራበት ወቅት በፍርድቤት ክርክር ምክንያት እርሻው እንዳይስተጓጎል መሆኑ ይነገራል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም በዝናባማው የክረምት ወቅት በሚሞሉ ወንዞች ምክንያት ሕዝቡ ፍርድቤቶች ለመቅረብ እንደሚቸግረው ታሳቢ በማድረግ እንደሆነም ይነገራል፡፡ ሆኖም ይኸው ጥንታዊ አሰራር በ21ኛው ክ/ዘመን በፌደራል ፍ/ቤቶች ቀጥሎ የተቋሙን አሰራር ለመደንገግ በ2013ዓ.ም በወጣው የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁ 1234 አንቀፅ 38 ስር ፍርድቤቶች በየአመቱ ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ዝግ ይሆናሉ ተብሎ ተመልክቷል፡፡ በዚሁ አንቀፅ ስርም ፍርድቤቶች ከስራ ውጭ በሆኑባቸው ጊዜያት በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ ዳኞች ተመድበው አስቸኳይ ጉዳዮችን እንዲያስተናግዱ ሊደረግ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

በፌደራል ፍ/ቤቶች ከሚታየው የመዝገብ መደራረብ እና መዘግየት ችግር እንዲሁም የተፋጠነ ፍትህ መስጠት ለህብረተሰቡ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር ቀደም ብሎ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የአርሶአደርን ሕይወት ታሳቢ ተደርጎ ይተገበር የነበረው ፍርድቤቶችን በክረምት ወቅት የመዝጋት ልማድ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተማዎች መቀጠሉን እንዴት ያዩታል? ሀሳቦትን ያካፍሉን!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!