በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት (DARS) የውክልና ሥልጣን (Power of Attorney) እንዴት መስጠት ይቻላል?

ለአንድ ሰው የውክልና ሥልጣን መስጠት ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ሕጋዊ ተግባር ነው። በፌዴራል ደረጃ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት (DARS) ውክልናን የማፅደቅ እና የመመዝገብን ስራ በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በክልሎች ይኸው ተግባር በፍትህ ቢሮዎች እና የዐቃቤሕግ ቢሮዎች ይሰራል። በፌዴራል ደረጃ በተለይም በአዲስ አበባ የሰነዶች ማረጋገጫ ፅ/ቤት አሠራሩን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል የቀየረ በመሆኑ፣ አሁን ላይ የውክልና ሰነዶችን በበይነመረብ (Online) ማዘጋጀትና ቀጠሮ መያዝ ግዴታ ሆኗል። ይህን ሒደት ያለ ምንም እንግልትና ስህተት እንዴት ማከናወን እንደሚችሉ ደረጃ በደረጃ እንመልከት።

1ኛ፡ ወደ ድረ-ገጹ መግባት፣ የውክልና አይነት መምረጥ እና የወካይን መረጃ መሙላት

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ማንኛውንም አገልግሎት ለመስጠት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን (Fayda ID) መጠቀምን ግዴታ አድርጓል።

ማሳሰቢያ፦ ውክልናው የሚሰጠው ድርጅትን ወይንም የንግድ ማህበርን በሚመለከት ከሆነ ወካዩ ይህንን ውክልና መስጠት እንደሚችል የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ወይም ቃለጉባዔ መቅረብ የሚገባው ሲሆን ዋና የንግድ ምዝገባ ከግለሰቡ መታወቂያ ጋር ኦሪጅናል እና ኮፒ መቅረብ ይኖርበታል።

2ኛ፡ የወኪሉን (Agent) መረጃ ማስገባት እና ስልጣኖችን መምረጥ

ለውክልና ሰጪው የተደረገው ተመሳሳይ የይለፍ ቃል ማረጋገጫ ሒደት ለወኪሉም (ውክልና ለሚቀበለው ሰው) ያስፈልጋል።

3ኛ፡ ረቂቁን ማረጋገጥ እና ማተም

4ኛ፡ በqetero.com የቀጠሮ ጊዜ መያዝ እና ክፍያ መፈጸም

ማሳሰቢያ፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያለ ቅድሚያ ቀጠሮ ማንኛውንም የሰነድ ማረጋገጥ ሒደት ሙሉ በሙሉ አቁሟል። ስለዚህ ሰነዱን ይዘው ከመሄድዎ በፊት ቀጠሮ መያዝ አለብዎት።

ይህንን ዲጂታል አሠራር መከተልዎ ጊዜዎን ከመቆጠቡም በላይ ሕጋዊ ጉዳይዎን ያለ ምንም እንግልት ለማስፈጸም ይረዳዎታል። ስለ ውክልና ሕጋዊ ውጤቶች እና የሥልጣን ወሰን ተጨማሪ ማብራሪያዎች ካስፈለግዎት የlawyer.et የሕግ ባለሙያዎችን ማማከር ይችላሉ።

Need Professional Legal Guidance?

Our team is ready to assist you with complex power of attorney drafting and legal due diligence.

Schedule Consultation
TELEGRAM WHATSAPP